አየሩ ለዐይን
ይይዛል….በብርሃን ነፀብራቅ ውበታቸው የሚገዛን የቀኑ ሙሽሮች ጠቆርቆር ብለዋል፡፡ ለወትሮው በሚያማምር የብረት ዘንግ ተከበው
በንፋሱ ግፊት ጣፋጭ በሆነው ለስላሳ ሙዚቃ የሚወዛወዙ አዲስ ሙሽሮች የሚመስሉት ዛፎች ውበታቸው ደብዝዞ ፀጥታ
ውጧቸዋል፡፡በአርምሞ ላይ ይመስላሉ፡፡ በዚህ የፀጥታ ወጀብ በፀጥታ መንጎዱ አስፈራኝ፡፡ ይልቅ ከእጅ ስልኬ ላይ ዘፈን ከፍቼ
መመሰጡን ምርጫዬ አደረኩት፡፡
የኔ ፍቅር….ለካ እንዲህ እወድሻለው
አብረን ሆነን መች አስቤው አውቃለው…….
ሙዚቃው ነው፡፡
እንደወትሮው የሙዚቃው መሳሪያ ቀድሞ ዘፋኙ ይከተላል ስል ዘፋኙ ቀድሞ መሪ ሆኖ አረፈው፡፡ የልጅ የመሰለ ቀጭን ድምፅ ሞቅ ብሎ
ጆሮ ላይ ሲስረቀረቅ እንደ ጅብ ጥላ ከብዶ ሰብሰብ ብሎ የነበረው ደመና በሞቅታው ሲበታተን…የሞቀው አየር በአፍንጫዬ ቁልቁል
ይተም ጀመር፡፡ ሞቅ አለኝ፡፡ ዙሪያዬን ከበው የሚያዜሙልኝ መላህክትን ያየው ያህል ደስ አለኝ፡፡
ዳገቱን ጨርሼ አውራ ጎዳናውን ተቀላቀልኩት፡፡ ዘፋኙ መዝፈኑን
ቀጥሏል፡፡
እንዲህ ይጨንቃል ሆይ አንቺን መሸኘቴ
ባዶ አረግሽኝ የእኔ አመቤቴ
ሳይታሰብ በድንገት
ልክ ልኬን
እየነገረኝ መሰለኝ….ደነገጥኩኝ…ከሳምንት በፊት ዘግቼው የነበረው አጀንዳ በእሊና የፍትህ ጓዳ ተቀሰቀሰ፡፡ ማን ይግባኝ ጠየቀ?
ታሳሳኝ የነበረችው የጠዋቷ ፀሐይ የልቤን ንግስት ላላስጨንቃት ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር፡፡