መቼም ስለ መርካቶ ያልተወራ
ነገር ያለ አይመስለኝም….መርካቶን የማያውቃት ይኖራል ለማለትም አልደፍርም፡፡ ከአፍሪካ በስፋቱ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ትልቁ የገበያ
ማህከል፡፡መርካቶ!
ስለ መርካቶ ሎሬት ፀጋዬ
ገ/መድህን በግጥም ‹‹አይ መርካቶ›› ተወዳጁ አብዱ ኪያር በዜማ ‹‹መርካቶ ሰፈሬ›› ና ወዘተ የብዙ የጥበብ ሰዎች እጅ ዳሷታል፡፡
እኔ የምለው መርካቶ
ውስጥ ካሉ ቦታዎች አውቶብስ ተራ አካባቢ የሚገኘውን አዲስ ከተማ ት/ቤትን አስተውለውት ያውቃሉ?
የቀድሞ ልዑል መኮንን
የአሁኑ አዲስ ከተማ መሠናዶ ት/ቤት የሠፈረበት አካካባቢ አስገራሚ ገፅታ ያለው ቦታ ነው፡፡ ት/ቤቱን ለተመለከተው እንዴት ሰው
ሊማርበት ይችላል ብሎ ሊገረም እንደሚችል ጥርጥር የለኝም፡፡ እመኑኝ በድፍን ኢትዮጵያ እንደ አዲስ ከተማ አስገራሚ ት/ቤት አይኖርም፡፡
ቀን በእውቀት የታነፁ
የአገር ተረካቢዎችን ለማፍራት የሚታትረው ት/ቤት ማታ ማታ በብዙ እንስቶች ተከቦ ይታያል፡፡
አንዳንዴ ዝም ብዬ ስመለከተው
ጠቢቡ ሰለሞንን የሆነ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ሁለቱም በሴት የመታጀባቸው ጉዳይ ነው፡፡
የዘመኑ ሰለሞን አዲስ
ከተማ አመሻሽ ላይ ልጅነታቸውን ባልጨረሱ ወጣት ሴቶች ተከቦ ማየቱ የተለመደ ነው፡፡