Friday, May 3, 2013

ፋሲካና ዶሮ


የፋሲካ በአል የአበሻ ምድር ላይ በተለየ መልኩ ከሚከበሩ በአላት ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ ይህን በአል ለየት የሚያደርገው ለአርባ ቀናት ከስጋና መሰል ምግቦች ተከልክሎ የከረመው የምህበኑ ሰውነት በአንድ ቀን ለሊት ውስጥ ያለ የሌለ አቅሙን አፈርጥሞ ለበቀል ሆዱን የሚያሰፋበት፤የእጆቹን መዳፍ  በቅባት የሚያረሰርስበት በአጠቃላይ ዶሮ በተባለች አዕዋፍ (እንስሳት) ላይ አብዮት የሚፈነዳበት የአብዮት በአል ነው፡፡ ወዳጄ የተሰመረባትን ሐረግ ሌላ ፍቺ እንዳይሰጧት እማጸኖታለው፡፡ ምናልባት በአሉ የድህነት እንጂ የአብዮት አይደለም ብሎ ሊሞግት የሚነሳ ካለ ባይደክም ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ የደህንነት በአል ለመሆኑ በሙሉ ልቤ አማኝ ስለሆንኩ….
ፋሲካችን ክርስቶስ በእለተ አሙስ ተይዞ ለፍርድ ወደ ጲላጦስ አደባባይ በሚወሰድበት ወቅት ለሚወደው ደቀ መዝሙሩ ዶሮ ሳይጮህ ሶስት ጊዜ ትክደኛለህ ብሌ ቀድሞ ተናግሮት እንደነበር ቅዱስ መፅሐፍ ይነግረናል፡፡ ቅዱሱ ሰው፤የቤተ ክርስቲያን የአለት መሰረት ታላቁ አዋርያ ጌታውን አላውቀውም ብሎ ሲክደው የክርስቶስን ቅድሚያ ትንቢት የቅዱስ ጴጥሮስን ክህደት ቆጥራ የመሰከረች ይህች ዶሮ ዛሬ ላይ ክፉኛ ተጨቁና ለፆም መፈሰኪያ መዋሏን ስናይ (በተለይ ለአቢሲኒያውያን) ነገሩ ምን ያህል ትስስር እንዳለው እንረዳለን፡፡ በቅዱስ ጴጥሮስ ፊት አውራሪነት የተመሰረተችው ቤተ ክርስቲያን ምዕመኖቿ ፋሲካቸውን በዶሮ መፈሰካቸው ምናልባትም ለምን አሽቃበትሽ በሚል የበቀል እርምጃ እየተወሰደባት ለመሆኖም ግምት ሰቶ ማለፍ ይቻላል፡፡

የታላቁን ቅዱስ ሰው አምላኩን መካድ ሶስት ጊዜ በመጮህ መመስከሯ እንደጥፋት ታይቶባት ከሆነ ከንፈር መምጠጥ ብቻ ሳይሆን አርነትም ልናወጣት ይገባል፡፡ በመላ አገሪቱ የሚገኙ ዶሮዎች በፋሲካ ምሽት ታላቅ ዘመቻ ይደረግባቸዋል፡፡ ዶሮዬ እራሷን ከዚህ ዘመቻ ለመታደግ ዋጋዋን ብታስወድድም ማን ሊሰማት…..ይበልጥ ዘመቻው ፉክክር በሚመስል መልኩ ተጧጡፎ በሷና በዘሯ (በተተኪ ዶሮዎች) እንቁላል ላይ ጭምር ከረር ብሏል፡፡
የዛሬ ሁለት ሺህ አመት ገደማ በሰልካካው ድምጧ የአምላክን በሚወደው ደቀ መዝሙር መካድ ደጋግማ በመጮህ ምስክርነቷን የሠጠችው ኋላም በጴጥሮስ እዝነ እሊና ደጋግማ በመጮህ ለንስሃ የጠራችው የያኔዋ የንስሃ አባት የአሁኗ መፈሰኪያ አቀኛዋ ዶሮ ነፃ ልትወጣ ይገባታል፡፡ በተለይ በዚህ በአል….ምክንያቱም የዛሬዋ ቀን ለሷ ታላቅ ቀን ነው፡፡ ለአምላኳ የቃል ማረጋገጫ (ትንቢት መፈፀሚያ) የሆነችበት ፤ቁም ነገር ሰርታ ያለፈችበት እለት ነውና እሷም(ዶሮ) ቀኑን በዶሮኛ ዘክራ የሰራችውን ታሪክ አስባ እንድትውል ብንፈቅድላት በሌላ በአል ስትበላ ምናልባት ጣፋጭነቷ ይበልጥ ሊጎላ ይችላል……
አርነት ለዶሮ

2 comments:

  1. mayekad ewenet new gen ledoro arenet yekebedal

    ReplyDelete
  2. may be ethiopians peoples think zt they avang hean. but the truth is they only use hean to fastig.
    i realy addmair ur point of veiw. (abel)

    ReplyDelete