የአንድ ሺህ ማይል ጉዞ
መጀመሪያው አንድ እርምጃ ነው የሚለውን አባባል ሰምተው ሊሆን ይችላል፡፡ እርሶም ይህን አንድ እርምጃ በመጀመርሆ እንኳን ደስ አልዎ!
እንደብዞዎች አኗኗር
ስልት ከሆነ ሕይወትዎ በጣም የተጨናነቀና ውጥረት የበዛበት ነው፡፡ ቢሆንም እባክሆ ለሚቀጥሉት ስድስት ቀናት ጊዜዎት ሰተውኝ ይህን
ፅሁፍ ያንብቡልኝ፡፡
ምን አልባት ነገሬን
ሳልጀምር ስለምን ላወራ እንደሆነ ገምተው አሊያም ሙሉ በሙሉ አውቀውት ሊሆን ይችላል፡፡ እባክሆ ሙሉ ፅሁፉን አንብበው ሳይጨርሱ
ምንም አይነት ፍርድ ለመስጠት አይቸኩሉ፡፡
እንጀምር…..
ነገሬን በጥያቄ ልጀምር
" ይህን ፅሁፍ ለምን እንደሚያነቡት ያውቃሉ?"
ምንአልባት መልስዎ ሊሆን
የሚችለው "ባጋጣሚ ብሎግህን ሰርች ሳደርግ አግኝቸው ነው" አሊያም "ጓደኛዬ ስለዚህ ፅሁፍ መረጃ ሰቶኝ
ነው" ወይም የተለያዩ አመክኖአዊ መልሶችን ሊሰጡኝ ይችላሉ፡፡
ዋናው ነገር መልስዎ
አመክኖአዊ ይሁንም አይሁንም ይህን ፅሁፍ የሚያነቡበት መሰረታዊ ነገር እንዳለ እሙን ነው፡፡ አንድ ነገር እየፈለጉ ነው! ነገር
ግን እስከ አሁን ድረስ በእይወትዎ ላይ ሊያመጣ ያለውን ነገር አላስተዋሉትም፡፡
ይህ ፅሁፍ ለእርስዎ
የሚሰጠው አንድ ነገር አለ ምናልባት በንግድ፤በጤናዎ፤በፍቅር እይወትዎ አሊያም ሊታይ የማይችል የአይምሮ ደስታ፡፡
አዕምርዎ በሕይወትዎ ውስጥ የፈለጉትን ሊያገኙበት የሚችሉበት ዋንኛውና ትልቁ ጉልበትዎ እንደሆነ
እስከ አሁን አልነገርኮትም፡፡ ሁሉም ሰው ጭንቅላት አለው ነገር ግን ስለምን አዕምሯቸውን ተጠቅመው የሚያልሙትን ሕይወት መኖር ተሳናቸው?
ለምን ብዙ ሰዎች የአዕምሯቸውን
ጉልበት ለራሳቸው ከመጠቀም ይልቅ እራሳቸውን ለማጥፊያነት ይጠቀሙበታል? መልሱን ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ያገኙታል፡፡ ትግስትዎ አይለየኝ፡፡
በመጀመሪያ
ስለወደፊትዎ አንድ ነገር ልተንብይ
በእርግጥ ሳይኪክ አይደለውም
ነገር ግን የእርስዎን መፃሂ ጊዜ ፍፁም እርግጠኛ ሆኜ መቶ በመቶ ልነግሮት ነው፡፡
እንዴት ይህን ላደርግ ቻልኩ?
በጣም ቀላል ነው፡፡
ስለእርስዎ በእርግጠኝነት አንድ ነገር አውቃለው፡፡ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኜ ስለእርስዎ ልናገር የሚያስችለኝን ነገር፡፡
ድሮ የምታስበውን እያሰብክ
የምጥቀጥል ከሆነ የምትሰራውም ነገር ድሮ ትሰራው የነበረውን ነው፡፡ ስለዚህም የምታገኘው ነገር በፊት ታገኘው የነበረውን ነው ማለት
ነው፡፡
በሌላ አነጋገር የአሁንና
የወደፊት ልምድህ ከዚህ በፊት ታስበው በነበረው ነገር ላይ መሰረት የጣለ ነው ማለት ነው፡፡ የእርስዎ የወደፊት ሕይወትዎ በአሁኗ
ደቂቃ በሚያስቧት ነገር የተወሰነችና ልትተነበይ የምትችል ናት፡፡ ስለዚህም የወደፊት ሕይወትዎን ማስተካከል ከፈለጉ በአሁኗ ደቂቃ
የሚያስቧትን አስተሳሰብ መቀየር የግድ ይሎታል፡፡
ይህን የሚያደርጉ ከሆነ የእርስዎን መፃሂ ጊዜዎን መተንበያ አያስቸግረኝም፡፡ በእርግጠኛነት ስኬታማና ፍፁም ደስተኛ ጊዜ ከፊትዎ ተደቅኗል፡፡
ይህን የሚያደርጉ ከሆነ የእርስዎን መፃሂ ጊዜዎን መተንበያ አያስቸግረኝም፡፡ በእርግጠኛነት ስኬታማና ፍፁም ደስተኛ ጊዜ ከፊትዎ ተደቅኗል፡፡
የትኩረት ሃይል
በዚህ ተከታታይ ፁሁፍ
ላይ ስለ ትኩረት ሃይል በሰፊው እናወጋለን፡፡
ስለሕይወትዎም ይሁን
በዙሪያዎ ስላለው ነገር የሚኖሮት አመለካከት ትኩረትዎ ካለበት ቦታ ላይ
መሰረት ያደረገ ነው፡፡
እስኪ ራስዎን ይህን
ጥያቄ ይጠይቁ " ብዙ ጊዜ ትኩረትዎ ምን ላይ ነው?" እርስዎ እንደሌላው ሰው ከሆኑ ስለ እርስዎ አስገራሚ ነገር
ያገኛሉ፡፡ ብዙ ጊዜዎን የማይፈልጉትን ነገር በማሰብና በመስራት ያሳልፋሉ፡፡
ለምን ይህ አስፈለገ?
ምክንያቱም ከፍላጎትህ
በተቃራኒው(የማትፈልገውን) እያሰብ የምትፈልገውን ልታገኝ አትችልም፡፡በምታስበው ነገር በቀላሉ የምትፈልገውን ነገር መፍጠርና ወደራስህ
መሳብ ይቻልሃል፡፡
ማረጋገጫ
እንዲህ ብለው አያውቁም?
"በጣም ጨንቆኛል፤ ነገር ግን ለምን እንደሆነ አላውቅም"
በሕይወትዎ መጥፎ ነገር፤ጭንቀት፤ተቃራኒ
ነገሮች ያለምክንያት ሊሰሙን እንደማይችሉ የሕይወት ተሞክሮዋችን ይነግረናል፡፡
የጭንቀት ስሜት ከተሰማህ
ሊያጨናንቅ የሚችል አስተሳሰ በውስጥህ ስላለና ጭንቀትን ስላሰብክ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የማትፈልገውን ነገር በማሰብህ ተጨንቀሃል፡፡
መጥፎ አሳብ በፍፁም
ጥሩ ነገርን አይፈጥርም፡፡ጥሩ አሳብም ውጤቱ መጥፎ አይሆንም፡፡
ሁሌም ስትጨነቅ፤ ስትፈራ፤ወይም
መጥፎ ነገር ሲገጥምህ የሁለት ምክንያቶች ውጤቶች ናቸው፡፡
1. ሊከሰትብህ በማትፈልገው ነገር ላይ ትኩረት በማድረግህ
2. ትኩረትህ ስለ መጪ ጊዜ በመሆኑ፡፡
ዘሬን
ስትኖር በምንም ተአምር ጭንቀት፤ ድብርት፤ ፍርሃት እንዲሁም መጥፎ ስሜት አይሰማህም፡፡ ለመጥፎ ስሜትህ መፈጠር ብቸኛው መንገድ
ምን ሊሆን ይችላል በሚል ስለወደፊቱ በመጨነቅ አሊያም ለወደፊት እንዳይከሰት ነማትፈልገው ነገር ትኩረትህን ማጣትህ ነው፡፡
ከዚህ
ፅሁፍ እስከሚቀጥለው ፅሁፍ ድረስ የቤት ስራ እንዲሰሩ እጠይቆታለው፡፡ አስተሳሰቦን ይፈትሹ፡፡ ብዙ ጊዜዎን ስለምን እያሰቡ እንደሚያሳልፉ
ያስተውሉ፡፡ በፍፁም ለመፍረድ እናዳይቸኩሉ፡፡ በአስተሳሰብዎ ላይ ፍተሻ ብቻ ያድርጉ፡፡
ስላለፈው
ነገር ትኩረት ያደርጋሉ? ስለ መጪ ጊዜዎ ይጨነቃሉ? ስለ ነገ ፤ስለ ሳምንት፤ ስለ ወር ያስባሉ?
where is next part? plese post the next article. ba z way it is good idea.
ReplyDelete