Saturday, May 25, 2013

የቡርቃ ዝምታ የተሰኘውን መፅሐፍ በነፃ ያነቡት

ጋዜጠኛና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ 
ከታዋቂውና ዝነኛው ጋዜጠኛና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ መፅሐፎች ውስጥ የቡርቃ ዝምታ የተሰኘውን መፅሐፍ በነፃ ያነቡት ዘንድ ተጋብዘዋል፡፡

1 comment:

  1. በመጀመርያ ጤናህ እነደምነው? እነኚያ የሚማምሩ ብእሮችህስ እንዴትናቸው?
    በመቀጠል የቡርቃ ዝምታ የተባለዉን መፅሃፍ ከማንበቤ በፊትና ካነበብኩት በሃላ ስላንተና ስለ መፅሃፉ ያለኝ ኣስተያየት እነደሚከተለው ላቀርብልህ ነው
    ከማንበቤ በፊት
    እኔ የትግራይ ሃገረሰለም ልጅነኝ! የዚሁው መፅሃፍህ ታሪክ ገና የ 10ኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ ሳለ መቀሌ ላይ ነው ኣንደ ሰው የነገረኝ ! እነዲህ ነበር ያለኝ
    እነ መለስ ዜናዉና በረከት ስምኦን ባገራቸው ልጅ( ኤርትራዊ ማለት ነው) ኢትዮያዊያን የሚበታትን መፅሃፍ ኣፃፉ ኣለኝ ያኔ 95 ዓ/ም ነበረ! እና እኔም ከነበረው የፖለቲካ ትኩሳት( ኢትዮ ኤርትራ ጦርነት) በመነሳት ኣመንካቸው! የቡርቃ ዝምታ የተባለዉን መፅሃፍ ገዝቸ ለማንበብም መቀሌ መፅሃፍት ቤት ፈለግኩኝ ኣንደ እንካ የለም ነበረ! ስለዘህ ድፍን 12 ዓመታት ኣንተና መፅሃፍህን ማናቸው ስል ከረምኩ ! በልቤ ግን የሻብያ ሰላይ እንደሆንክ ስል ተወራ ይህን ሰላይነትህን እሰከ የደራሲዉና የጋዜጠኛው ማስታወሻ እስካነብበት ድረሰ የሻብያ ሰላይ ኣድርጌ እወስድህ ነበር! ዳሩ የተሳሳትኩ መሆኑ የገባኝ ግና ሁለቱም ማስታወሻዎች መፃፍክን ካነበብኩ በሃላ ነበረ!
    የቡርቃ ዝምታ ካነበብኩ በሃላ
    የቡርቃ ዝምታ እዉነት ያለው ትምቢታዉ ኣፈታሪክ ይመስላል!ኣኖሊና ሀዉኒ በኦሮሞዎች ላይ ድፍን 100 ዓመታትነ የተበደሉትና የደረሰባቸው የሞራልና የስነልቦና በደል ግልፅ ነው! እንዲህ ስልህ መፃሃፍህን ድርሰት ኣለመሆኑና በእዉነተኛ ታሪክ ላይ የተመረኮዘ ብየ ስላመንኩ ነው! ለምሳሌ ኣብዛኛው ኦሮሞዎች ስማቸው በኦሮምኛ እንዲሆን ኣለመፈለጋቸው በገሃዱ ኣለምም የነበረ ነው! ስለ ኦሮሞ ነፃነትና ስለ ኣማራው ነፍጠኝነት በስፋት የዳሰስው ይህን መፃፍ በኦሮሞዎችና በኣማረዎች ለሚቀጥሉት 100 ዓመትም ግጭት ሊኖር እንደሚችል ሀዉኒ ስትናገር ይደመጠል! ይህ ጉዳይ በሃገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ተደምሮበት የጭን ላይ ቁስል መሆኑን መርሳት የለብህም! ምክንያቱ ሰዎች የሚረዱልህ ኣማራና ሮሞዎች ለመነጣጠል እንጂ ያለፈዉን እዉነተኛ ታሪክ ነው ብለው ለያምኑህ ይችላል!
    በተረፈ ግን ወያኔ የሻብያ ሰላይ የምትለዋን ቅፅል መለጣጠፍ ባህሪው ስል ሆነ ማሰብ ኣይገባህም!
    ሌላ ቀን ደግሞ ስለ የጋዜጠኛዉና የደራሲው ማስታወሻ ያለኝ ኣመለካከት እፅፍልሃለዉ!
    ዉሾች ይጮሃሉ ግመሎቹ ይጋዛሉ!

    ReplyDelete