Sunday, December 22, 2013

የሮበርት አንቶኔ ሕይወትን የመቀየሪያ ምስጢሮች

የአንድ ሺህ ማይል ጉዞ መጀመሪያው አንድ እርምጃ ነው የሚለውን አባባል ሰምተው ሊሆን ይችላል፡፡ እርሶም ይህን አንድ እርምጃ በመጀመርሆ እንኳን ደስ አልዎ!
እንደብዞዎች አኗኗር ስልት ከሆነ ሕይወትዎ በጣም የተጨናነቀና ውጥረት የበዛበት ነው፡፡ ቢሆንም እባክሆ ለሚቀጥሉት ስድስት ቀናት ጊዜዎት ሰተውኝ ይህን ፅሁፍ ያንብቡልኝ፡፡
ምን አልባት ነገሬን ሳልጀምር ስለምን ላወራ እንደሆነ ገምተው አሊያም ሙሉ በሙሉ አውቀውት ሊሆን ይችላል፡፡ እባክሆ ሙሉ ፅሁፉን አንብበው ሳይጨርሱ ምንም አይነት ፍርድ ለመስጠት አይቸኩሉ፡፡
እንጀምር…..
ነገሬን በጥያቄ ልጀምር " ይህን ፅሁፍ ለምን እንደሚያነቡት ያውቃሉ?"
ምንአልባት መልስዎ ሊሆን የሚችለው "ባጋጣሚ ብሎግህን ሰርች ሳደርግ አግኝቸው ነው" አሊያም "ጓደኛዬ ስለዚህ ፅሁፍ መረጃ ሰቶኝ ነው" ወይም የተለያዩ አመክኖአዊ መልሶችን ሊሰጡኝ ይችላሉ፡፡
ዋናው ነገር መልስዎ አመክኖአዊ ይሁንም አይሁንም ይህን ፅሁፍ የሚያነቡበት መሰረታዊ ነገር እንዳለ እሙን ነው፡፡ አንድ ነገር እየፈለጉ ነው! ነገር ግን እስከ አሁን ድረስ በእይወትዎ ላይ ሊያመጣ ያለውን ነገር አላስተዋሉትም፡፡
ይህ ፅሁፍ ለእርስዎ የሚሰጠው አንድ ነገር አለ ምናልባት በንግድ፤በጤናዎ፤በፍቅር እይወትዎ አሊያም ሊታይ የማይችል የአይምሮ ደስታ፡፡
አዕምርዎ በሕይወትዎ  ውስጥ የፈለጉትን ሊያገኙበት የሚችሉበት ዋንኛውና ትልቁ ጉልበትዎ እንደሆነ እስከ አሁን አልነገርኮትም፡፡ ሁሉም ሰው ጭንቅላት አለው ነገር ግን ስለምን አዕምሯቸውን ተጠቅመው የሚያልሙትን ሕይወት መኖር ተሳናቸው?
ለምን ብዙ ሰዎች የአዕምሯቸውን ጉልበት ለራሳቸው ከመጠቀም ይልቅ እራሳቸውን ለማጥፊያነት ይጠቀሙበታል? መልሱን ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ያገኙታል፡፡ ትግስትዎ አይለየኝ፡፡
በመጀመሪያ ስለወደፊትዎ አንድ ነገር ልተንብይ
በእርግጥ ሳይኪክ አይደለውም ነገር ግን የእርስዎን መፃሂ ጊዜ ፍፁም እርግጠኛ ሆኜ መቶ በመቶ ልነግሮት ነው፡፡
እንዴት ይህን ላደርግ ቻልኩ? 
በጣም ቀላል ነው፡፡ ስለእርስዎ በእርግጠኝነት አንድ ነገር አውቃለው፡፡ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኜ ስለእርስዎ ልናገር የሚያስችለኝን ነገር፡፡
ድሮ የምታስበውን እያሰብክ የምጥቀጥል ከሆነ የምትሰራውም ነገር ድሮ ትሰራው የነበረውን ነው፡፡ ስለዚህም የምታገኘው ነገር በፊት ታገኘው የነበረውን ነው ማለት ነው፡፡
በሌላ አነጋገር የአሁንና የወደፊት ልምድህ ከዚህ በፊት ታስበው በነበረው ነገር ላይ መሰረት የጣለ ነው ማለት ነው፡፡ የእርስዎ የወደፊት ሕይወትዎ በአሁኗ ደቂቃ በሚያስቧት ነገር የተወሰነችና ልትተነበይ የምትችል ናት፡፡ ስለዚህም የወደፊት ሕይወትዎን ማስተካከል ከፈለጉ በአሁኗ ደቂቃ የሚያስቧትን አስተሳሰብ መቀየር የግድ ይሎታል፡፡
 ይህን የሚያደርጉ ከሆነ የእርስዎን መፃሂ ጊዜዎን መተንበያ አያስቸግረኝም፡፡ በእርግጠኛነት ስኬታማና ፍፁም ደስተኛ ጊዜ ከፊትዎ ተደቅኗል፡፡
የትኩረት ሃይል
በዚህ ተከታታይ ፁሁፍ ላይ ስለ ትኩረት ሃይል በሰፊው እናወጋለን፡፡
ስለሕይወትዎም ይሁን በዙሪያዎ ስላለው ነገር የሚኖሮት አመለካከት ትኩረትዎ ካለበት ቦታ ላይ  መሰረት ያደረገ ነው፡፡
እስኪ ራስዎን ይህን ጥያቄ ይጠይቁ " ብዙ ጊዜ ትኩረትዎ ምን ላይ ነው?" እርስዎ እንደሌላው ሰው ከሆኑ ስለ እርስዎ አስገራሚ ነገር ያገኛሉ፡፡ ብዙ ጊዜዎን የማይፈልጉትን ነገር በማሰብና በመስራት ያሳልፋሉ፡፡
ለምን ይህ አስፈለገ?
ምክንያቱም ከፍላጎትህ በተቃራኒው(የማትፈልገውን) እያሰብ የምትፈልገውን ልታገኝ አትችልም፡፡በምታስበው ነገር በቀላሉ የምትፈልገውን ነገር መፍጠርና ወደራስህ መሳብ ይቻልሃል፡፡
ማረጋገጫ
እንዲህ ብለው አያውቁም? "በጣም ጨንቆኛል፤ ነገር ግን ለምን እንደሆነ አላውቅም"
በሕይወትዎ መጥፎ ነገር፤ጭንቀት፤ተቃራኒ ነገሮች ያለምክንያት ሊሰሙን እንደማይችሉ የሕይወት ተሞክሮዋችን ይነግረናል፡፡
የጭንቀት ስሜት ከተሰማህ ሊያጨናንቅ የሚችል አስተሳሰ በውስጥህ ስላለና ጭንቀትን ስላሰብክ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የማትፈልገውን ነገር በማሰብህ ተጨንቀሃል፡፡
መጥፎ አሳብ በፍፁም ጥሩ ነገርን አይፈጥርም፡፡ጥሩ አሳብም ውጤቱ መጥፎ አይሆንም፡፡
ሁሌም ስትጨነቅ፤ ስትፈራ፤ወይም መጥፎ ነገር ሲገጥምህ የሁለት ምክንያቶች ውጤቶች ናቸው፡፡
1.   ሊከሰትብህ በማትፈልገው ነገር ላይ ትኩረት በማድረግህ
2.   ትኩረትህ ስለ መጪ ጊዜ በመሆኑ፡፡
ዘሬን ስትኖር በምንም ተአምር ጭንቀት፤ ድብርት፤ ፍርሃት እንዲሁም መጥፎ ስሜት አይሰማህም፡፡ ለመጥፎ ስሜትህ መፈጠር ብቸኛው መንገድ ምን ሊሆን ይችላል በሚል ስለወደፊቱ በመጨነቅ አሊያም ለወደፊት እንዳይከሰት ነማትፈልገው ነገር ትኩረትህን ማጣትህ ነው፡፡
ከዚህ ፅሁፍ እስከሚቀጥለው ፅሁፍ ድረስ የቤት ስራ እንዲሰሩ እጠይቆታለው፡፡ አስተሳሰቦን ይፈትሹ፡፡ ብዙ ጊዜዎን ስለምን እያሰቡ እንደሚያሳልፉ ያስተውሉ፡፡ በፍፁም ለመፍረድ እናዳይቸኩሉ፡፡ በአስተሳሰብዎ ላይ ፍተሻ ብቻ ያድርጉ፡፡

ስላለፈው ነገር ትኩረት ያደርጋሉ? ስለ መጪ ጊዜዎ ይጨነቃሉ? ስለ ነገ ፤ስለ ሳምንት፤ ስለ ወር ያስባሉ?

Wednesday, November 13, 2013

ዳግማዊ ሠለሞን!

መቼም ስለ መርካቶ ያልተወራ ነገር ያለ አይመስለኝም….መርካቶን የማያውቃት ይኖራል ለማለትም አልደፍርም፡፡ ከአፍሪካ በስፋቱ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ትልቁ የገበያ ማህከል፡፡መርካቶ!
ስለ መርካቶ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን በግጥም ‹‹አይ መርካቶ›› ተወዳጁ አብዱ ኪያር በዜማ ‹‹መርካቶ ሰፈሬ›› ና ወዘተ የብዙ የጥበብ ሰዎች እጅ ዳሷታል፡፡
እኔ የምለው መርካቶ ውስጥ ካሉ ቦታዎች አውቶብስ ተራ አካባቢ የሚገኘውን አዲስ ከተማ ት/ቤትን አስተውለውት ያውቃሉ?
የቀድሞ ልዑል መኮንን የአሁኑ አዲስ ከተማ መሠናዶ ት/ቤት የሠፈረበት አካካባቢ አስገራሚ ገፅታ ያለው ቦታ ነው፡፡ ት/ቤቱን ለተመለከተው እንዴት ሰው ሊማርበት ይችላል ብሎ ሊገረም እንደሚችል ጥርጥር የለኝም፡፡ እመኑኝ በድፍን ኢትዮጵያ እንደ አዲስ ከተማ አስገራሚ ት/ቤት አይኖርም፡፡
ቀን በእውቀት የታነፁ የአገር ተረካቢዎችን ለማፍራት የሚታትረው ት/ቤት ማታ ማታ በብዙ እንስቶች ተከቦ ይታያል፡፡
አንዳንዴ ዝም ብዬ ስመለከተው ጠቢቡ ሰለሞንን የሆነ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ሁለቱም በሴት የመታጀባቸው ጉዳይ ነው፡፡
የዘመኑ ሰለሞን አዲስ ከተማ አመሻሽ ላይ ልጅነታቸውን ባልጨረሱ ወጣት ሴቶች ተከቦ ማየቱ የተለመደ ነው፡፡
እዚህ ጋር ጥበብና ሴት ያላቸውን ግንኙነት እንድናስተውል ይጋብዘናል…ሁለቱም የሆነ አይነት ዝምድና ያላቸው ይመስላል፡፡ የሚገርመው ምንም እንኳን ት/ቤቱ በአስቸጋሪ አካባቢ ላይ ቢገኝም ለዘመናት በእውቀት አሰጣጡ ተስተካካይ ማጣቱ ደግሞ ይበልጥ አግራሞታችንን ይጨምረዋል፡፡
ዘፋኙ ‹‹ የምንነጋገርበት ቋንቋው አንድ አይነት 
        አዲስ ከተማ ነው የተማርንበት››
አንድ ሠሞን ት/ቤቱ ይነሳል ተብሎ በነበረበት ወቅት ‹‹መርካቶ ምድር ገንዘብ እንጂ እውቀት ምን ሊረባ›› ብለው የሚያስቡ ቱባ የመርካቶ ባለሀብቶች ትልቅ የገበያ ማዕከል ለማድረግ ቢቋምጡም ዳግማዊ ሠለሞንን ማን ደፍሮት ከነክብሩ ቀን በተማሪዎች ማታ በእንስቶች ተከቦ ዘላለማዊነቱን እያሳበቀ ዘሬም ድረስ አለ፡፡ ማታ ላይ የት/ቤቱ ደጃፍ በታዋቂ የአገራችን ሰዎች በተዋቡ ጋዜጣና በፅሔቶች  ምንጣፍ ወለሉን ሸፍነው የንባብን ጥማት ሊቆርጡ ይታትራሉ፡፡ እንቡጥ እንስቶች ደግሞ አጥሩን በመውረር ሴትነታቸውን ለገበያ የሚያቀርቡበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ የቀኑ ያ የእውቀት አውድማ አመሻሹ ላይ የወሲብ መናኽሪያ ይቀየርና ት/ቤት ደርሶ የማያውቅ እግር ሁላ በስሜት እየተነዳ አዲስ ከተማ ት/ቤት ከቸች ይላል፡፡ ት/ቤቱ በራፍ ላይ በትልቁ ‹‹ ኑ ብርሃንን ተቀበሉ ሂዱናም አንፀባርቁ›› የሚለውን ጥቅስ  ለተማሪዎች በመተው ‹‹ ኑ የጭኔን በረከት ተቀበሉ ሂዱናም ዝናዬን አውሩ›› በመል ተቀይሮ ሌቱ ቀን ይሆናል፡፡ በመርካቶ ፀሐይ አትጠልቅም ያለው ማን ነበር? ሠላም ባልትና ወይስ አዲስ ከተማ ት/ቤት?
ዙሪያው በማህበራዊ ቀውሶች የተከበበው ይህ ት/ቤት ግቢው እጅግ በስነ ምግባር የታነፁ ጠማሪዎች ያሉበትና ውጤታማ የሆነ ለመሆኑ ምስክር አያሻንም፡፡
ከፖሊስ ጋር አይጥና ድመት  ሆነው ስራቸውን የሚሰሩት እንስቶች አንዳንዴ የፖሊስ ደረቅ ጎማ መቅመስ የግድ ይላቸዋል፡፡ ምክንያቱም ከት/ቤቱ ፊት ለፊት የሚገኘው ጠባብ ቅያስ በሕጋዊ ሴተኛ አዳሪዎች የተሞላ ስለሆነ እኚህ አጥር ጥግ ሞገደኛውን ወንድ የሚጠባበቁ እንስቶች ሕገ-ወጥ ተብለው መሆኑ ነው….እኒህ ሁሉ በዳግማዊ ሰለሞን የየእለት ተግባራት ናቸው፡፡
መርካቶ!!


Saturday, May 25, 2013

የቡርቃ ዝምታ የተሰኘውን መፅሐፍ በነፃ ያነቡት

ጋዜጠኛና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ 
ከታዋቂውና ዝነኛው ጋዜጠኛና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ መፅሐፎች ውስጥ የቡርቃ ዝምታ የተሰኘውን መፅሐፍ በነፃ ያነቡት ዘንድ ተጋብዘዋል፡፡

Friday, May 24, 2013

A Little Joke


The pope dies and goes to heaven. At the pearly gates, St. Peter welcomes him and asks if he's ready to enter heaven for all eternity. The pope replies, "Yes, but before I go in, I would really like to see what hell is like."
St. Peter thinks a moment and then responds, "I suppose it would be okay if you went down there for a half hour or so."
With that, the pope finds himself in hell, where, to his amazement, the inhabitants are having a huge party. They have the best of the best spread out: French champagne, Italian food, and music of all sorts, from Lawrence Welk to Jimi Hendrix. As the pope watches everyone eating, drinking and being merry, he starts to become very hungry and cannot wait to go back to heaven.
When the pope returns, St. Peter asks him, "How was hell?"
The pope replies, "Well, they were having such a big feast, I became famished watching them."
St. Peter then asks if the pope is ready to enter heaven, to which the pope replies, "Oh yes, I'm very excited. If the people in hell are having such a good time, I cannot imagine how great heaven will be!"
With that, St. Peter leads the pope into a small white room with a small white table and white chairs, and instructs the pope to have a seat. The pope looks a little puzzled but abides his host.
After a few minutes, Jesus enters the room carrying a peanut butter sandwich and a glass of milk, and takes a seat.
A moment later, St. Peter enters bearing two peanut butter sandwiches and glasses of milk. He hands a peanut butter sandwich and glass of milk to the pope, and sits down and starts to eat.
As they silently sit eating, the pope becomes more and more agitated, until St. Peter finally asks him why he is not eating.
"Well," the pope responds, "down in hell they are having a big bash, with all the finest food, drink, music and dancing. I imagined heaven would top even that!"
"Why," St. Peter queries, raising his eyebrows, "you don't expect us to do all that for just the three of us, do you?"

Friday, May 3, 2013

ፋሲካና ዶሮ


የፋሲካ በአል የአበሻ ምድር ላይ በተለየ መልኩ ከሚከበሩ በአላት ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ ይህን በአል ለየት የሚያደርገው ለአርባ ቀናት ከስጋና መሰል ምግቦች ተከልክሎ የከረመው የምህበኑ ሰውነት በአንድ ቀን ለሊት ውስጥ ያለ የሌለ አቅሙን አፈርጥሞ ለበቀል ሆዱን የሚያሰፋበት፤የእጆቹን መዳፍ  በቅባት የሚያረሰርስበት በአጠቃላይ ዶሮ በተባለች አዕዋፍ (እንስሳት) ላይ አብዮት የሚፈነዳበት የአብዮት በአል ነው፡፡ ወዳጄ የተሰመረባትን ሐረግ ሌላ ፍቺ እንዳይሰጧት እማጸኖታለው፡፡ ምናልባት በአሉ የድህነት እንጂ የአብዮት አይደለም ብሎ ሊሞግት የሚነሳ ካለ ባይደክም ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ የደህንነት በአል ለመሆኑ በሙሉ ልቤ አማኝ ስለሆንኩ….
ፋሲካችን ክርስቶስ በእለተ አሙስ ተይዞ ለፍርድ ወደ ጲላጦስ አደባባይ በሚወሰድበት ወቅት ለሚወደው ደቀ መዝሙሩ ዶሮ ሳይጮህ ሶስት ጊዜ ትክደኛለህ ብሌ ቀድሞ ተናግሮት እንደነበር ቅዱስ መፅሐፍ ይነግረናል፡፡ ቅዱሱ ሰው፤የቤተ ክርስቲያን የአለት መሰረት ታላቁ አዋርያ ጌታውን አላውቀውም ብሎ ሲክደው የክርስቶስን ቅድሚያ ትንቢት የቅዱስ ጴጥሮስን ክህደት ቆጥራ የመሰከረች ይህች ዶሮ ዛሬ ላይ ክፉኛ ተጨቁና ለፆም መፈሰኪያ መዋሏን ስናይ (በተለይ ለአቢሲኒያውያን) ነገሩ ምን ያህል ትስስር እንዳለው እንረዳለን፡፡ በቅዱስ ጴጥሮስ ፊት አውራሪነት የተመሰረተችው ቤተ ክርስቲያን ምዕመኖቿ ፋሲካቸውን በዶሮ መፈሰካቸው ምናልባትም ለምን አሽቃበትሽ በሚል የበቀል እርምጃ እየተወሰደባት ለመሆኖም ግምት ሰቶ ማለፍ ይቻላል፡፡
የታላቁን ቅዱስ ሰው አምላኩን መካድ ሶስት ጊዜ በመጮህ መመስከሯ እንደጥፋት ታይቶባት ከሆነ ከንፈር መምጠጥ ብቻ ሳይሆን አርነትም ልናወጣት ይገባል፡፡ በመላ አገሪቱ የሚገኙ ዶሮዎች በፋሲካ ምሽት ታላቅ ዘመቻ ይደረግባቸዋል፡፡ ዶሮዬ እራሷን ከዚህ ዘመቻ ለመታደግ ዋጋዋን ብታስወድድም ማን ሊሰማት…..ይበልጥ ዘመቻው ፉክክር በሚመስል መልኩ ተጧጡፎ በሷና በዘሯ (በተተኪ ዶሮዎች) እንቁላል ላይ ጭምር ከረር ብሏል፡፡
የዛሬ ሁለት ሺህ አመት ገደማ በሰልካካው ድምጧ የአምላክን በሚወደው ደቀ መዝሙር መካድ ደጋግማ በመጮህ ምስክርነቷን የሠጠችው ኋላም በጴጥሮስ እዝነ እሊና ደጋግማ በመጮህ ለንስሃ የጠራችው የያኔዋ የንስሃ አባት የአሁኗ መፈሰኪያ አቀኛዋ ዶሮ ነፃ ልትወጣ ይገባታል፡፡ በተለይ በዚህ በአል….ምክንያቱም የዛሬዋ ቀን ለሷ ታላቅ ቀን ነው፡፡ ለአምላኳ የቃል ማረጋገጫ (ትንቢት መፈፀሚያ) የሆነችበት ፤ቁም ነገር ሰርታ ያለፈችበት እለት ነውና እሷም(ዶሮ) ቀኑን በዶሮኛ ዘክራ የሰራችውን ታሪክ አስባ እንድትውል ብንፈቅድላት በሌላ በአል ስትበላ ምናልባት ጣፋጭነቷ ይበልጥ ሊጎላ ይችላል……
አርነት ለዶሮ

Wednesday, April 24, 2013

የኢሰፓ ሊቀመንበር የነበሩት ኮሎኔል መንግስቱ በልብ በሽታ .መሞት.....menegestu
Mengestu h/mariam with Fidel kastero
የዛሬ የማህበራዊ ድህረ ገፅ ወሬዎች በቀድሞ የኢሰፓ ሊቀመንበር በነበሩት ኮሎኔል መንግስቱ ሃ/ማርያም ሆኗል፡፡ ኮሎኔሉ በልብ በሽታ እነደሞቱ ጥቂት የማይባሉ የማህበራዊ ድህረ ገፅ ታዳሚዎች መርዶውን እየነገሩን ነው፡፡ የኮሎኔሉን መሞት መንግስት ከዘረጋው መልካም አስተዳደር የመነጨ ስለመሆኖም አንዳንዶች እየደሰኮሩ ስንሰማ ባላንጣችንን ሞት ክብር ላንተ እንድል አስገድዶናል፡፡ መንግስቱ ደግም ሰሩ ክፉ የዚህች ድሃ አገር ገዥ ሆነው ለ 17 አመታት ኖረዋል፡፡ በመሞታቸው መደሰት ሳይሆን እንሲቪላይዝድ ሰው ቤተሰባቸውን ባናፅናናም ክፉ መናገሩን በበኩሌ የማልደግፈው ነው፡፡ አትዮጵያ ባትቀድምም አትዮጵያ ትቅደምን እንድናዜም ያረጉ ሶሻሊስት ኢትዮጵያን ለመገንባት ግንባር ድረስ የሄዱ ትጉህ ወታደር ኋላም ጥሩ ፈርጣጭ ነበሩና የእውነት ሞተው እንኳን ቢሆን ነብሳቸውን ይማርልን ብለን ኢትዮጵያዊ ጨዋነታችንን እናሳይ እላለው፡፡

Sunday, April 14, 2013

አበሻ ኩሩ ነው!?

የትኛው አበሻ? የድሮው ወይስ የአሁኑ? እውን በምናችን ይሆን እንዲ አበሻ ኩሩ ነው በሚል ብሂል ውጥርጥር ያልነው፡፡ ቲሸርቶቻችን የሚናገሩት ስለኩሩነታችን፤ስለጀግንነታችንና ስለብዝሃነታችን ከሆነ ሰንበትበት ብሏል፡፡ኩሩ ማህበረሰብ ለራሱ የተለየ ቦታ ያለውና ሌሎች ላይ የማይደርስ በሎሎች የተከበረ ለመሆኑም የማህበረሰብ ሳይንስ ሊቃውንት የሚስማሙበት አቅ ነው፡፡
የአበሻ ኩሩነት እንደቻይናውያን እንቁራሪት አለመብላቱና ምግብ መምረጡ ከሆነ ኩሩነት ትርጉሙ መቀየር አለበት ባይ ነኝ፡፡ ኩሩነታችን አለመንበርከካችንና በነጭ አለመገዛታችን  ነው የምንል ከሆነ ደግሞ ለዚህ ዘመን አበሾች የማይመጥን ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ነጮች እንደዋዛ ክብራችንን ከነጠቁን ዘመናት አለፉ....በቱሪስት መዳረሻ በሆኑ ከተሞቻችን  ኩሩው አበሻ ለፈረንጆች የሚያሳየውን ፍቅር ስንመለከት ሰውኛ የሆነ የጨዋ ሕዝብ ልዩ ምልክት መሆኑን እንታዘብና ወደራሳችን ተመልሰን ጓዳችንን ስናይ የሰውኛ ባህሪ መሆኑ ይጠፋብንና አድር ባይነታችን ይጎላብናል፡፡ ሴቶቻችን የአበሻ ወንድ በአፍንጫዬ ካሉም ሰንበትበት ብለዋል...ቄሶቻችን በቤተ እምነት መዘክር ውስጥ ‹‹ፈረንጅ መቷል ውጡ›› ማለት ከጀመሩም አመታት አለፉ፡፡ ማለፍ ክልክል ነው፤መንገዱ ዝግ ነው በሚባሉ ቦታዎች ላይ አበሾች ተኮልኩለው ነጭ እንደዋዛ ሲያልፍና ፍቃድ ሲሰጠው ስናይ ልማታዊነታችን ታውሶን በቸልታ የምናልፈው የእለት ተእለት ተራ ጉዳይ ከሆነም ሰንብቷል፡፡ ኩሩነት በአባቶች ታሪክ መታበይ ከሆነ እውነት ኩሩ አለመሆናችንን ላስረግጥ እወዳለው፡፡
የአበሻ ኩሩነት በጎዳና የወደቀውን ወንድሙን የሚያንቋሽሽና አለውልህ ከማለት የኘጮችን በጎነት የሚናፍቅ እከሌ እኮ እስፖንሰር አግኝቶ....የምንል የጉድ ልጆች ከንቱ ኩራት... ሲረግጡን የምንረገጥ የራሳችን ማንነት የጠፋብን ተአምር ጠባቂዎች፤የምላስ ቁማርተኞች፤ሆዳችን ክብራችን የሆነ ዘመነኛ ኩሩዎች!
ወዳጄ ኩሩ ነኝ ብለህ ታስባለህ? እንግዲያውስ ለራስህ ቦታ ይኑርህ፤እራስህን አክብር፤ በቆዳ ልዩነት የማታምን ቅድሚያ ለኢትዮጵያዊው ወንድሜ የሚል አትዮጵያዊ ብሔርተኛ ሁን!!
በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ወደፊት በሰፊው እናወጋለን፡፡